|
አገልጋዮችም፣አጥቢያዎችም፣
ማኅበራትም
ኅብረታቸውን
ሊያገኙት
የሚችሉት
በራሳቸው
ሳይሆን
እንደ
መልካም
የወይን
ዘለላ
ከምትሸከማቸው
ግንድ
ከቤተ
ክርስቲያን
ነው፡፡
ቤተ
ክርስቲያን
ራስዋ
ክርስቶስ
እርሷም
አካሉ
ናትና፡፡
ጌታችን
ስለ
ወይን
ግንድ
እና
ፍሬ
ባስተማረበት
አንቀጽ
የግንዱን
እና
የቅርንጫፉን
ግንኙነት
ሲያስረዳን
«ቅርንጫፍ
በወይኑ
ግንድ
ባይኖር
ከራሱ
ፍሬ
ሊያፈራ
እንዳይቻለው
እንዲሁ
እናንተ
ደግሞ
በእኔ
ባትኖሩ
ትችሉም፡፡
እኔ
የወይን
ግንድ
ነኝ፡፡
እናንተም
ቅርንጫፎች
ናችሁ»
ብሎናል
/ዮሐ.15÷4/::
አንዱ
ሻኩራ
ለብቻው
ከግንዱ
ተነጥሎ
የሚያደርገው
አገልግሎትም
ሆነ
ጩኸት
ቤተ
ክርስቲያናዊ
እንደማይሆነው
ሁሉ
አገልጋዮችም
ሆኑ
አጥቢያዎች
በአንዲቱ
ቤተ
ክርስቲያን
አማካኝነት
ኅብረት
አንድነት
ፈጥረው
ካልጮኹ
ካላገለገሉ
በቀር
አገልግሎታቸው
ግላዊ
እንጂ
ቤተ
ክርስቲያናዊ
ለመሆን
አይችልም፡፡
አባቶቻችን
በካህናት
እጅ
መሥዋዕተ
ዕጣን
የሚቀርብበትን
ጽንሐሕ
በቅዳሴም
ሆነ
በሌሎች
ጸሎቶች
ጊዜ
አገልግሎት
ላይ
እንዲውል
እና
ለእይታችን
ቅርብ
እንዲሆን
ካደረጉባቸው
ምክንያቶች
አንዱ
አንድነታችንን
አዘውትረን
ማሰብ
እንድንችል
እና
ስለ
አንድነታችንም
እንድንጸልይ
ነው፡፡
እኛ
ወይም
አጥቢያችን
በጽንሐሑ
ላይ
እንደሚገኙት
ሻኩራዎች
ነን፡፡
ከግንዱ
ከተነጠልን
እንወድቃለን፡፡
ስለዚህም
ፈሬ
ለማፍራት
እንድንችል
እንደ
ሻኩራዎቹ
በአንድነት
እናገልግል፡፡
|