|
በአለንበት
አገር በሰሜን
አሜሪካ፤
በሀገራችን
በኢትዮጵያና
በልዩ ልዩ
አኅጉራት
የምትገኙ
አባቶቼና
እናቶቼ
ወንድሞቼና
እኅቶቼ ከሁሉ
አስቀድሞ
ለጥበቃዉና
ለመግቦቱ
ወሰን
የሌለበት
ልዑል
እግዚአብሔር
በረድኤት
ጠብቆ ሰላም
እርቅ
ለተመሠረተበት
ሰውና
መላእክት
በአንድነት
ለዘመሩበት
እንኳን
ለብርሃነ
ልደቱ በሰላም
አደረሳችሁ
በማለት
በሀገረ
ስብከቱ ስም
መልካም
ምኞቴን
አቀርባለሁ።
“ነአምር
ከመ ኵሉ
ዘተወልደ
እምነ
እግዚአብሔር
ኢይኤብስ አላ
ዘተወልደ እም
እግዚአብሔር
የአቅብ ርእሶ
ወእኩይኒ
ኢይስሕጦ”
ከእግዚአብሔር
የተወለደ ሁሉ
እንደማይበድል
እናዉቃለን
ከእግዚአብሔር
የተወለደ
ራሱን
ይጠብቃል
እንጂ ክፉም
አይነካዉም
፩ዮሐ ፭፡፲፰
በብርሃነ
ልደቱ ክብርና
ሞገስን
የተጎናፀፋችሁ
አባቶቼና
እናቶቼ
ወንድሞቼና
እኅቶቼ
እንዲሁም
ከቂም በቀል
ከተንኮል
ከክፋት
ንጹሐን
የሆናችሁ
የመንፈስ
ቅዱስ ልጆቼ
ሕጻናት፤በአጠቃላይ
በክርስቶስ
ክርስቲያን
የተሰኛችሁ
ወገኖቼ
በሙሉ፤ከዚህ
በላይ
በተጠቀሰዉ
መልእክት
ክርስቲያኖች
ከእግዚአብሔር
በመወለድ
የአገኘነውንና
ወደፊትም
የምናገኘዉን
ክብርና ስጦታ
ነጻነትና ድል
አድራጊነት
ሐዋርያው
ሲአስረዳን
“ከእግዚአብሔር
የተወለደ
ራሱን
ይጠብቃል
እንጂ ክፉም
አይነካውም”
ይላል በጥንተ
ተፈጥሮ የሰው
ልጅ
ከእግዚአብሔር
የተሰጠውን
ጸጋና ክብር
በኀጢአት
ምክንያት
በመቀማቱና
በመራቆቱ
ራሱን
የመጠበቅና
ክፉውን
የመከላከል
ብቃት አንሶት
የተሰጠውን
መመሪያና ሕግ
ጥሶ ለምን
እንደተፈጠረና
ማን
እንደፈጠረዉ
ዘንግቶ
በምክረ ከይሲ
ተታሎ
እግዚአብሔርን
በደለ።
በዚህም
ምክንያት
ከክብሩ
ተዋረደ፡
የተሰጠዉም
ፀጋ ተገፈፈ፡
በኑሮዉም ሁሉ
ተቅበዝባዥና
ስደተኛ
ሆነ፡ስለሆነም
የሰዉ ልጅ
ኑሮ
በውርደትና
በጉስቁልና
ይቀጥል ዘንድ
እግዚአብሔር
ስላልወደደ፤
የሰው ልጅ፤
በደል
የማይፈጽምበትን፤
ራሱን
የሚጠብቅበትን፤
ከክፉ
የሚርቅበትን፤በሚያልፈውም
ዓለም ይሁን፡
በማያልፈው
ዓለም፤
በፍቅርና
በደስታ
የሚኖርበትን
መንገድ
በማስተካከል
እግዚአብሔር
ለሰው ልጅ
በገባዉ ቃል
ኪዳን መሠረት
“የዘመኑ
ፍጻሜ
ሲደርስ”ከሦስቱ
አካላት አንዱ
እግዚአብሔር
ወልድ በተለየ
አካሉ
ያለአባት
በመንፈስቅዱስ
ግብር
ከቅድስተ
ቅዱሳን
ከድንግል
ማርያም
በቤተልሔም
ተወለደ።በመሆኑም
ርቆ የነበረዉ
የሰው ልጅ
ወደ
እግዚአብሔር
ቀረበ
ከቅዱሳን
መላእክትም
ጋር
ለማመስገን
ቻለ።
ከባርነትም
ተላቆ በልደቱ
ልጅነትን
አገኘ
ከእግዚአብሔር
የተወለደውንም
ሁሉ ክፉ
እንደማይነካዉ
በቃለ
እግዚአብሔር
ተረጋገጠ።
ቅዱስ መጽሐፍ
እንዲህ ሲል
እንደተናገረ
“እስመ ኵሉ
ዘተወልደ እም
እግዚአብሔር
ይመዉዖ
ለዓለም”
ከእግዚአብሔር
የተወለደ ሁሉ
ዓለምን
ያሸንፈዋል።
፩ዮሐ ፭፡ ፬
በክርስቶስ
ክርስቲያን
በወልድ ዉሉድ
የተሰኛችሁ
ወገኖቼ
ትንቢተ
ነቢያት
ይፈጸም ዘንድ
መድኃኒታችን
ኢየሱስ
ክርስቶስ
ከሰማየ
ሰማያት
ወርዶ፤ በቤተ
ልሔም
በከብቶች
በረት
የተወለደበትን፤
ትህትናዉንና
ፍቅሩን
ያሳየበትን፤
ለአምላክነቱ
ክብር የጥበብ
ሰዎች
የገበሩበትን፤
ሰዉና
መላእክት
በአንድነት
የዘመሩበትን፤
ከባርነት
ተላቀን
ልጅነት
ያገኘንበትን፤
ዓመተ ኵነኔ
ዓመተ ፍዳ
አክትሞ
፤ዓመተ
ምህረት
የተመሠረተበትን፤
የሰው ልጆች
ነጻነት
የታወጀበትን፤
በማሰብ
በአለ ልደቱን
ስናከብር
“አኀዊነ
ለንትፋቀር
በበይናቲነ
እስመ ተፋቅሮ
እምነ
እግዚአብሔር
ውእቱ ወኵሉ
ዘይትፋቀር
እምነ
እግዚአብሔር
ውእቱ ተወልደ
ወየአምሮ
ለእግዚአብሔር”
ወንድሞች ሆይ
ርስ
በእርሳችን
እንፋቀር
ፍቅር
ከእግዚአብሔር
የተገኘ
ነዉና፤
የሚፋቀር ሁሉ
ከእግዚአብሔር
ተወልዶአል።
እግዚአብሔርንም
ያዉቀዋል።፩ዮሐ
፬፡፯
የሚለውን ቃለ
እግዚአብሔር
በማስታወስ
በመካከላችን
ያለዉን
አለመግባባት
በማስወገድ፤
ሽንገላና
ምጸት
በሌለበት፤
በፍጹም ፍቅር
ለመኖርና
ለመመላለስ
በመወሰን፤
የአምላካችንና
የመድኀኒታችን
የኢየሱስ
ክርስቶስን
በዓለ ልደት
ልናከብር
ይገባናል።በዓሉንም
ስናከብር
በአንዳንዶች
ዘንድ እንደ
ተለመደዉ
በልማድ
ሳይሆን
የአምላካችንን
ፍቅሩንና
ዉለታዉን
እያሰብን
ስለአደረደገልን
ሁሉ
የቸርነቱን
ሥራ
እያደነቅን
ልናከብረዉ
ይገባል።
ከዚህም
ጋር “ዘመኑን
ዋጁ”
እንደተባለው
የክርስትና
ደሴት ተብላ
በዓለም
መድረክ
በተመሰከረላትና
በተረጋገጠላት
በሀገራችን
በኢትዮጵያ፤
ቤተ
ክርስቲያናችን
በኢአማንያን
እና
በአክራሪዎች
እየተፈተነች
ያለችበት
ወቅት ነዉና፤
ከላይ
እንደተገለጸዉ
የተራራቅን
ተቀራርበን፤
ለችግሮች ሁሉ
መፍትሄዎችን
በማፈላለግ
በአንድነት
ቤተ
ክርስቲያናችንን
እንጠብቅ፡
በሃይማኖት
በምግባር
ጎልብተን፤
ለእናት
ኦርቶዶክሳዊት
ቤተ
ክርስቲያናችን
አለን
ልጆችሽ፡
እንበላት፤
ዛሬም
እንደቤተልሔሙ
በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያናችን
ጥላ ሥር ተሰባስበን
ስብሐት
ለእግዚአብሔር
በሰማያት
ወሰላም
በምድር
ሥምረቱ
ለሰብእ
እያልን
እንዘምር።በአንጻሩም
ተከባብሮ
የመኖር፤
ኢትዮጵያዊ
ባህላችን እና
ሥርዓታችን፤
ወጋችን እና
ልማዳችን
ባልሆነ
መንገድ
እንዳይበከል
፤ የጥንቱ
የጥዋቱ
ተባብሮ
የመኖር
ወገናዊ
ፍቅራችን፤
ወደነበርነት
እንዳይለወጥ፤
ልናስብበትና
ልንወያይበት
ያስፈልጋል።
የተወደዳችሁ
ወገኖቼ
ከእግዚአብሔር
የተወለደ ሁሉ
እንደማይበድል
የበደሉንን
ይቅር
በማለት፤
የበደልናቸዉንም
ይቅርታ
በመጠየቅ፤
ራሳችንንም
ሆነ ቤተ
ክርስቲያናችንን
ከክፉ
እንጠብቅ፡
መልካም ልደት
ለሁላችን።በድጋሜ
እንኳን
ለበርሃነ
ልደቱ
አደረሳችሁ
እንደምንኖርበት
አገር ዘመን
አቆጣጠርም
እንኳን
ለአዲሱ አመት
በሰላም እና
አደረሳችሁ።
አምላካችን
እግዚአብሔር
ለሀገራችን
ለኢትዮጵያ
እና ለመላዉ
ዓለም ሰላሙን
ይስጥ።
ብፁዕ
አባ አብርሃም
ሊቀ
ጳጳስ
|