:::ዜናዎች:::

:::ያግኙን :::


ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፤ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት፤ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት

ርዕሰ አንቀጽ

ወጣቱ ወዴት ነው መሄድ ያለበት)
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሃይማኖት ፍቅር በነደዱ፣ ለተጋድሎ ራሳቸውን በሰጡ የአባቶቻቸውን ታሪክ ለመድገም በቆረጡ ታሪክ ሠሪ ወጣቶች የተሞላ ነው፡፡ እነ አቤልን፣ እነ ይስሐቅን፣ እነ ያዕቆብን፣ ነቢዩ ዳንኤልን እና ሠለስቱ ደቂቅን፣ ባሮክን እና አቤሜሌክን በብሉይ ኪዳን እናገኛቸዋለን፡፡Ý
ተጨማሪ

 
 
  ራእይ
 
የጥያቄዎ መልስ
  ሊቀ ጳጳሱን ይጠይቁ
 
 
 
 

ቢቻላችሁስ ዐይኖቻችሁን አውጥታችሁ በሰጣችሁኝ ብየ እምሰክርላችዋለሁ  በቀሲስ ነህምያ ጌቱ
 
በፈተና የሚፀና እሱ ይድናል  በቀሲስ ብርሃኑ ጎበና 
የቤተክርስቲያነ አስተዳደራዊ መዋቅር 

  የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ምን ለምን እንዴት 

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትና የአንድነት ፍሬ በተለያዩ አጋጣሚዎች ታይቷል፡፡ይሁን እንጂ አንድነቱ የተጠናከረ ባለመሆኑ የተከሰቱ ችግሮችም አሉ፡፡ ለአንድነቱ መላላት ምክንያት የሆኑቱን በሁለት ከፍሎ መመልከት መልካም ነው ፡፡እነርሱም ዉጫዊና ዉስጣዊ ችግሮች ናችዉ፡፡

ተጨማሪ

ብጹዕ አቡነ አብርሃም የአዲ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ
መስከረም ፩ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም  

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን

በሀገራችን በኢትዮጵያ በአለንበት ሀገር በሰሜን አሜሪካ እንዲሁም በመላዉ ዓለም የምትገኙ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኛችሁ እና ኢትዮጵያዉን ወገኖቼ በሙሉ፤ ከሁሉ አስቀድሞ እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደዘመነ ማቴዎስ አሸጋገራቹሁ፤ በአለፈዉም ዓመት በረድኤት ጠብቆ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ አዲሱ ዓመት የፍቅርና የደስታ የሰላምና የአንድነት የዕዉቀትና የብልጽግና የሕይወትና የጤና ዘመን ይሆንላችሁ ዘንድ ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን በማለት ልባዊ ምኞቴን በሀገረ ስብከቱ ስም ስገልጽ በታላቅ ደስታ ነዉ።

ተጨማሪ

 
መኑ አንተ? አንተ ማነህ?  

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሃይማኖት ለወለደቻቸዉ  ልጆቿ ብቻ ሳትወሰን  ለኢትዮጵያዉያን ወገኖቿ ሁሉ የመጀመሪያዉን ትምህርት ቤት በመክፈት ሥነ ጽሑፍን[፣ ሥነ ጥበብን፣ ሥነ ስዕልን፣ አስተዳደርን፣ በብቃትና  በትጋት አስተምራለች። ከዚህም ጋር በጋራ የአገር ድንበር መጠበቅን፣ በሀዘን በደስታ ተባብሮና ተደጋግፎ መኖርን፣ ለትዉልድ ሁሉ አበርክታለች።  አበዉ እንደሚሉት ታሪክ ትልቅ ትምህርት ቤት ከመሆኑም በላይ መስተዋት ነዉና ከመልካም ታሪኳ እንደተማርነዉና እንደተረዳነዉ እዉነተኛ ልጆቿን ለይታ የምታዉቅ በመሆኗ መልካም ስምን ሰጥታ ሞግስን እና ክብርን አጎናጽፋ ትልቅ ትንሽ፣ ነጭ ጥቁር፣ ሩቅ ቅርብ፣ ዘመድ ባዕድ ሳትለይ እናትነቷን አዉቀዉ፣ ጥሪዋን ሰምተዉ፣ ሥራቷን ተቀብለዉ፣ ሕጓን አክብረዉ ለሚመላለሱት ሁሉ አድልዎ በሌለበት የእናትነት ፍቅሯ የማይጠፋ የዘለዓለም ስምና ክብር ከድል አክሊል ጋር አቀዳጅታለች። 

 

ሀገረ ስብከቱን ለመደገፍ የተጠራ ዝግጅት ተካሄደ

ዋሽንግተን ዲሲ (ነሐሴ 17/2000 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዲሲና አካባቢውን ሀ/ስብከት አቅም ለማጎልበት የተጠራ ዝግጅት በውጤት ተጠናቀቀ፡፡ቅዳሜ ነሐሴ 17/ 2000 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ በተዘጋጀው በዚህ ዝግጅት የሀገረ ስብከቱ 

ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃምና የሰሜን ምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ተገኝተው ትምህርት፣ ምክርና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በትምህርታቸው ‹‹ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ›› (ማቴ 19፡17) የሚለውን አምላካዊ ቃል በመጥቀስ ሰፊ ትምህርት የሰጡ ሲሆን የእመቤታችንን በዓል ለማክበር ከሄዱበት ሐዋርያዊ አገልግሎት ሲመለሱ ዕረፍት ላግኝ ሳይሉ ወደ ጉባዔው የመጡት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስም በበኩላቸው የተጀመረው ታላቅ ሥራ እንዲቀጥልና ከግብ እንዲደርስ ሁሉም እንዲራዳ በሰጡት አባታዊ ምክር አሳስበዋል፡፡
በጉባዔው ላይ የተገኙ ምእመናን የእጅ እና የአንገት ወርቃቸውን ሳይቀር በመለገስ ሀገረ ስብከቱ ሥራውን እንዲጀምርና ታላቋ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በውጪው ዓለም የምትፈጽመው ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲሳካ ያላቸውን መልካም ምኞት ገልጸዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ የተጠየቁ ምእመናን ሀገረ ስብከቱ እንዲህ ያለውን ተመሳሳይ ዝግጅት ማካሄዱን እንዲቀጥልበት አሳስበዋል፡፡


  ከሻኩራው ሰንማር        

ካህኑ መሥዋዕተ ዕጣኑን በሚያቀርብበት በጽንሐሑ ሦስት ገመዶች ላይ ተንጠልጥለው የሿሿቴ ድምፅ የሚያሰሙት ክብ ቅርጾች ሻኩራ ይባላሉ፡፡ ሦስቱ የብረት ገመዶች የሥላሴ ምሳሌ ሲሆኑ ገመዶቹ ከላይ አንድ መሆናቸው የአንድነታቸው ምሳሌ ነው፡፡ እነዚህ ሻኩራዎች አጠቃላይ ቆጥራቸው 24 ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ያለማቋረጥ የሚያመሰግኑት የካህናተ ሰማይ የሱራፌል ምሳሌዎች ናቸው፡፡እነዚህ ሻኩራዎች በብረት ገመዱ ላይ ሆነው ካልሆነ በስተቀር በየራሳቸው አገልግሎት አይኖራቸውም፡፡ ምሳሌነታቸውም አይገለጥም፡፡

ተጨማሪ

አሐቲ  

‘’ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ እንተ ሐዋርያት፣ የሐዋርያት ጉባኤ በምትሆን፣ከሁሉም በላይ በሆነች በንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን ” 

በማለት በቁስጥንጥንያ የሰበሰቡ 150 አባቶች እንደ መሠከሩት ስለ ቤተ ክርስቲያን ስንናገር አራቱ ነገሮች ማለትም አንዲት፣ ቅድስት፣ከሁሉም በላይ የሆነች፣ ሐዋርያዊት የሚሉትን መመስከር አለብን። 
ተጨማሪ

የኒዉዮርክ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና አመሠራረት ታሪክ

ታሪክ ታማኝነትን እዉነትን ሊያጨስብጥና ሊያስዳስስ የሚችለዉ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የጥንቱን ዘመን በማሰብ፣ ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ ጀምሮ ከአበዉ ወደ ልጅ ልጅ የተሸጋገሩትን ዘመናት ወደ ኋላ መለስ ብሎ በዐይነ ሕሊና በማየትና በመቃኘት ከአባት ጠይቆ በመረዳት ከሽማግሌዎች ጠይቆ እዉነተኛ ታሪክን በመያዝ ነው

ተጨማሪ

 if you can't read this website click here and install the font. 

ገረ ስብከታችን

 
  Biblical
  Patristic
  Others
  Listen Lesson of the week
  Listen Mesbak of the week
  Downlad Songs and Publications
  Discover Ethiopian Orthodox Church History
  Preaching of the week
 
  www.eotc-patriarch.org
  www.eotc-mkidusan.org
 
www.mahiberekidusan.org
  www.tewahedomedia.org
 
www.tewahedo.org
 
www.kidistselassie.org 
Home| Feedback| Webmaster
EOTC-DC Diocese., All Rights Reserved